አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት Addis Ababa City Bus Service Enterprise

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት Addis Ababa City Bus Service Enterprise የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት አዋጅ ቁጥር74/2014 እንዲሁም በደንብ ቁጥር 144/2015 የተቋቋመ የልማት ድርጅት ነው።

  "የቴክኒክ ባለሞያዎች የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ልምምድ ለማድረግ የሚያስችል የእውቀት ሸግግር እየተደረገ መሆኑ የድርጅታችንን የቴክኒክ አቅም ከፍ ያደርገዋል" ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አ...
20/03/2023



"የቴክኒክ ባለሞያዎች የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ልምምድ ለማድረግ የሚያስችል የእውቀት ሸግግር እየተደረገ መሆኑ የድርጅታችንን የቴክኒክ አቅም ከፍ ያደርገዋል" ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው አለሙ የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ሲያደረጉ ገልጸዋል።

በእውቀት የተደገፈ ጥገና ለአዳዲሶቹ አውቶቡሶችን ለማድረግ እና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ የሚያሰችል ስልጠና እየሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የግብአት አቅርቦት እና የቴክኒክ ምርት አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ ኢ/ር አዳነ አብደታ አብራርተዋል ።

ዘመናዊነትን ተረድተው ፈጣንና ውጤታማ የሆነ ጥገና ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ከሃይገር ካንፖኒ በመጡ ባለሞያዎች ለጅርጅቱ የቴክኒክ ባለሞያዎች እየተሰጠ እና የእውቀት ሽግግር አየተደረገ መሆኑ የቴክኒክ ምርት አገልግሎት ዳይሬክተርነት ዳይሬክተር አቶ እሱያውቃል መላኩ ገልፀዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘው እንደገለፁት ስልጠናው በዙር ለሁሉም የቴክኒክ ባለሞያዎች እንደሚሰጥና ITS ፣ ኤሌክትሪክ ፣አውቶማቲክ ትራንስሚሽን ፣ኤር ብሬክ ሲስተም ፣አንቲ ብሬክ ሎክ ሲስተም እና የመሳሰሉትን ለጥገና ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ የንድፈ ሃሳብና የተግባር ላይ ልምምድ እና ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አብራርተዋል።

  የአንድ ተቋም የአገልግሎት ጥራት ሊመጣ የሚችለው ተቋሙ በሚኖረው የሰለጠነ እና ብቃት ያለው የሰው ሃይል መሆኑን ይታመናል። በስልጠና የሚያምነው  የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ...
17/03/2023



የአንድ ተቋም የአገልግሎት ጥራት ሊመጣ የሚችለው ተቋሙ በሚኖረው የሰለጠነ እና ብቃት ያለው የሰው ሃይል መሆኑን ይታመናል።

በስልጠና የሚያምነው የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የአገልግሎት ጥራትን ለመጨመር እና ተቋማዊ አሰራርን ለማዘመን የሚያግዘውን ለ5,000 ሰራተኞቹ ስልጠና አሰናድቶ በመስጠት ላይ ነው፡፡

በዚህ ሰፊ የስልጠና ፕረግራም ላይ በዘርፉ አንቱ የተባሉ ምሁራኞች በማሰልጠን ላይ ሲሆኑ ከእነዚህ ምሁራኞች መካከል የድርጅታችን ም/ዋና ስራ አስኪያጅና የፋይናስና ገቢ ምንጭ ማጎልበት ዘርፍ ሃላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ አንዱ ናቸው፡፡

 "የውሰጥና የውጭ ባለጉዳይና ደንበኞቻችን ሊገለገሉ ሲመጡ የመገልገለ ና የመናገር (የመጠየቅ) መብት እንዳላቸው እኛ አገልጋዮች ደግሞ የማስተናገድ እና የማዳመጥ ግዴታ እንዳለብን አውቀን መስ...
16/03/2023



"የውሰጥና የውጭ ባለጉዳይና ደንበኞቻችን ሊገለገሉ ሲመጡ የመገልገለ ና የመናገር (የመጠየቅ) መብት እንዳላቸው እኛ አገልጋዮች ደግሞ የማስተናገድ እና የማዳመጥ ግዴታ እንዳለብን አውቀን መስራት አለብን"።

አቶ ግዛው አለሙ
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ

  ከጅማሬው ገና ከጥንስሱ ሰልጣኔን አሀዱ ብለን ስንተዋወቅ በመጀመሪያው አውቶቡስ ጎዳና ላይ አገልግሎት ይዘን ብቅ አልን። እነሆ አመታትን ተሻግረን ዘንድሮ ላይ ከዘመኑ ጋር የተናበቡ ለህዝብ...
13/03/2023



ከጅማሬው ገና ከጥንስሱ ሰልጣኔን አሀዱ ብለን ስንተዋወቅ በመጀመሪያው አውቶቡስ ጎዳና ላይ አገልግሎት ይዘን ብቅ አልን።

እነሆ አመታትን ተሻግረን ዘንድሮ ላይ ከዘመኑ ጋር የተናበቡ ለህዝብ ምቾት የሚሰጡ አውቶቡሶችን ይዘን አገልግሎት ላይ አለን።

ከዘመኑ ጋር አብረን ተጉዘን ዛሬ ላይ ደርሰናል
ነገን በተሻለ አብረን ለመጎዝ ስንዱ ሆነን እንቀርባለን።

 ።ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ስልጠናቸውን አጠናቀው የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበረከተላቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለሶስተኛ ጊዜ ለአገልግሎት ሂሳብ ተቀባይና ካፒቴኖች...
12/03/2023



ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ስልጠናቸውን አጠናቀው የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበረከተላቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለሶስተኛ ጊዜ ለአገልግሎት ሂሳብ ተቀባይና ካፒቴኖች ያዘጋጀውን ስልጠና በብቃት ላጠናቀቁ ከአምስቱም ቅርንጫፍ ለተውጣጡ 300 ሰራተኞቹ የምስጋና ምስክር ወረቀት አበረከተ።

በመረሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ከሰራተኞቹ ውይይት ያደረጉት የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው አለሙ ከሰራተኝው ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።

  ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በሚገባ ስልጠናቸውን አጠናቀው የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበረከተላቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የደንበኛን ፍላጎት መሰረት ያደረገ አገልግሎ...
09/03/2023



ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በሚገባ ስልጠናቸውን አጠናቀው የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበረከተላቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የደንበኛን ፍላጎት መሰረት ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዘውን ስልጠና ለ300 ካፒቴን እና አገልግሎት ሂሳብ ተቀባዮች ለሁለተኛ ዙር መስጠቱን የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው አለሙ ገለፁ።

ዋና ስራ አስኪያጁ በስራ አመራር ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለውን ስልጠና ላጠናቀቁ የድርጅቱ ሰራተኞች ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት "ደንበኛን ሊያረካ የሚችል አገልግሎት በመስጠት ተገልጋዮቻችንን ማሰደሰት አለብን ብለዋል።

ተሳታፊ ሰልጣኞች በበኩላቸው እንደዚህ አይነት ስልጠና ድርጅቱ ማዘጋጀቱን አድንቀው በቀጣይም ለሌሎች የድርጅቱ ሰራተኞች ቢሰጥ ሲሉ ተናግረዋል።

  " ስልጠናው የረሳንውን እንድናስታውስ ከማድረግ ባለፈ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ የፈጠረልን በመሆኑ፤ በቀጣይ የተሻለ ስራ እንድንሰራ እና ደንበኞቻችን በጥሩ ሞያዊ ስነ-ምግባር...
08/03/2023



" ስልጠናው የረሳንውን እንድናስታውስ ከማድረግ ባለፈ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ የፈጠረልን በመሆኑ፤ በቀጣይ የተሻለ ስራ እንድንሰራ እና ደንበኞቻችን በጥሩ ሞያዊ ስነ-ምግባር እንድናገለግል አቅም ፈጥሮልናል" ፡፡ ሰልጣኞች

  ለመላው የድርጅታችን እንስት ሰራተኞች እና ደንበኞቻችን በሙሉ እንኳን ለአለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) አደረሳችሁ!!በከተማችን ብሎም በሃገራችን የልማት እና መልካም አስተዳደር እ...
08/03/2023



ለመላው የድርጅታችን እንስት ሰራተኞች እና ደንበኞቻችን በሙሉ እንኳን ለአለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) አደረሳችሁ!!

በከተማችን ብሎም በሃገራችን የልማት እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም ተቋማዊ ዕድገት ላይ የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ እንደሆነ የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ያምናል።

ድርጅታችን የጀመረውን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት፣ የህብረተሰብ ዕርካታን የማሳደግ ጉዞ ላይ የሴቶች ተሳትፎና ሚና የጎላ በመሆኑ ሁልጊዜም ቢሆን አሳታፊ አድርገን እንሰራልን።

በቀጣይ ሴት አሽከርካሪዎቻችን እና በሁሉም የስራ ዘርፎች ላይ ያሉ እህቶቻችንን በይበልጥ በማበርታትና በመደገፍ አቅማቸውን በማሳደግ የተቋማችንን ራዕይ እናሳካለን።

ለመላው የድርጅታችን እንስት ሰራተኞቻች በሙሉ እንኳን ለዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉን በጠንካራ የሴትነት አቅም እንድናሳልፍ መልዕክቴን በታላቅ አክብሮት ማስተላለፍ እወዳለሁ።

ወ/ሮ ገነት ወልዴ
የህግና ሰው ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ

'' " አቶ ግዛው ዓለሙ  283 የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ድርጅቱ ያዘጋጀውን  ስልጠና በተገቢ በማጠናቀቃቸው የተሳትፎ የምስክር ወረቀት  ተበረከተላቸው። አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግ...
08/03/2023

'' " አቶ ግዛው ዓለሙ

283 የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ድርጅቱ ያዘጋጀውን ስልጠና በተገቢ በማጠናቀቃቸው የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበረከተላቸው።

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለደንበኞች፤ ፈጣን፣ ምቹና ዘመናዊ የሆነ አገልግሎት ለህብረተስቡ ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል ያለውን ስልጠና ለአገልግሎት ሂሳብ ተቀባይና ካፒቴኖች እየሰጠ ሲሆን በዚህም በመጀመሪያ ዙር ሰልጠናቸውን ያጠናቀቁ ባለሞያዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ከሰልጣኞች ጋራ ውይይት ያደረጉ ሲሆን "በውይይቱ ላይ የተገኙት የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ዓለሙ ለተሳታፊዎች "ተገልጋዮቻችን አማራጭ ስላጡ እና ተቸግረው ሳይሆን መርጠውን እንዲገለገሉ ማድረግ አለብን" ሲሉ አደራ በማለት ተናግረዋል።

  የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለ5 ሽህ የአገልግሎት ሂሳብ ተቀባይ እና ካፒቴኖች ስልጠና  እየሰጠ ነው። ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ጋር በመተባበር ፤በመንገድ ትራፊክ...
07/03/2023



የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለ5 ሽህ የአገልግሎት ሂሳብ ተቀባይ እና ካፒቴኖች ስልጠና እየሰጠ ነው።

ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ጋር በመተባበር ፤በመንገድ ትራፊክ አደጋና አደጋን ተከላክሎ የማሽከርከር ስልት፣የአሽከርካሪ ባህሪ እና ሞያዊ ስነ-ምግባር፣ እና ደንበኛ አያያዝ ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የድርጅቱ ፋይናስና ገቢ ምንጭ ማጎልበት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ ገልፀዋል።

የተሻለ አገልግሎት ለህብረተሰባችን በማቅረብ የደንበኛን እርካታን ለማሳደግ ድርጅታችን ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ጋር የሚሰጠው ስልጠና በዙር የሚሰጥ መሆኑንና ሁሉንም ሰራተኛ ተሳታፊ እንደሚያደርግ የሰው ሀይል አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ገነት ወልዴ ተናግረው የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ዛሬ እንደሚያጠናቅቁ ገልፀዋል።

Adresse

22 Mazorea/equatorial Guinea Street (adjacent To Mekelit Building), Addis Ababa
Democratic Republic Of The

Site Web

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት Addis Ababa City Bus Service Enterprise publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Contacter L'entreprise

Envoyer un message à አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት Addis Ababa City Bus Service Enterprise:

Partager